"ሁላችሁም ልጆች ናችሁ፤ ሀገሪቱን እንዳታጠፏት!"
"ሁላችሁም ልጆች ናችሁ፤ ሀገሪቱን እንዳታጠፏት!" "--ኃይለስላሴ ከስልጣናቸው ወርደው አራተኛ ክፍለጦር ከሚገኘው ቪላቤት ከገቡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኟቸው ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም ነበሩ ፤ በኮሌኔል ዳንኤል አስፋው ፣ በሻለቃ አስራት ደስታ እና በሻምበል ፍስሀ ገዳ ታጅበው አጠገባቸው እንደደረሱ እርሳቸውን ለመጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው መኮንኖች ሳይመስሏቸው አልቀሩም። "ጅኒናር አማን የታለ ? ከትንሽ አንስተን ለታላቅ ደረጃ ባበቃነው.... "አሉ በቁጭት። "ጄኔራል አማን የሉም" ብለው ሻለቃ መንግስቱ መልስ ሲሰጡ ከአፋቸው ነጠቅ አድርገው "ሁላችሁም ልጆች ናችሁ ፤ የሰራችሁት የልጅነት ስራ ነው ፤ስለሀገራችሁ የምታውቁት ነገር የለም ፤ ሀገሪቱን እንዳታጠፏት" ብለው ተናገሩ። በእርግጥም እንደህዝብ አስተዳዳሪ ሀገራችንን ያወቅናት ዘግይተን ችግሯ እየተጫነን በሄደ ቁጥር ነበር…
Read the full story at addis_news ↗