ተጠባቂው የአርሰናልና ማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

ADDIS_REPORTERneutral2026-11-29 19:20:43 UTC
AdYour ad here[email protected]

ተጠባቂው የአርሰናልና ማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት በኢሚሬትስ ስታዲየም የሊጉ መሪ አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል። 34ኛው ደቂቃ ላይ ኤርሊንግ ሃላንድ ሲቲን መሪ ያደረገች ግብ ሲያስቆጥር፣ 40ኛው ደቂቃ ላይ ካይ ሃቨርት አርሰናልን አቻ አድርጎ ለእረፍት ወጥተዋል። ሃላንድ በአምስት ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ነው አርሰናል ላይ ግብ ያስቆጠረው። ከእረፍት መልስ 48ኛው ደቂቃ ላይ ኤንዞ ፈርናንዴዝ ያስቆጠራት ግብ ማንቸስተር ሲቲን ወደ መሪነት ብትመልስም፣ ጁሪየን ቲምበር 83ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ አርሰናልን ከሽንፈት ታድጋ ነጥብ ተጋርቶ እንዲወጣ አድርጋለች። በውጤቱም አርሰናል ለተከታታይ 12 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ግስጋሴውን ሲቀጥል፣ ነጥቡን 29 አድርሶ የደረጃ…

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]