በሀሰተኛ ሰነድ ማጭበርበር ወንጀል ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የነበሩት ቀሲስ በላይ መኮንን ከእስር መፈታታቸው ተገለጸ።

ADDIS_REPORTERneutral2026-09-02 19:05:06 UTC
AdYour ad here[email protected]

በሀሰተኛ ሰነድ ማጭበርበር ወንጀል ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የነበሩት ቀሲስ በላይ መኮንን ከእስር መፈታታቸው ተገለጸ። ​ቀሲስ በላይ ከ 2 አመት የእስር ቆይታ በኋላ ዛሬ ጠዋት ከእስር ተፈተው በአሁኑ ሰዓት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል። ​ግለሰቡ በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 6 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማውጣት በመሞከራቸው፣ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የአምስት ዓመት እስራት እና የ10 ሺህ ብር ቅጣት ተፈርዶባቸው የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ​ከእሳቸው ጋር አብረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ሌሎች ሁለት ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው የአራት ዓመት እስራት እና የ3 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸው እንደነበር አይዘነጋም። ተከሳሾቹ የወንጀል ሕጉን እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ…

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]