ቶኩማ ሀርቨስቲንግ የተባለ የግብርና ማሽን የሠራው ወጣት 👏

TIKVAHUNIVERSITYneutral2026-09-03 08:14:33 UTC
AdYour ad here[email protected]

ቶኩማ ሀርቨስቲንግ የተባለ የግብርና ማሽን የሠራው ወጣት 👏 ሰለሞን ቡታ ከፍቼ ከተማ የተገኘ የክህሎት ኢትዮጵያ ውድድር ቴክኖሎጂ ፈጣሪ ወጣት ነው፡፡ "ቶኩማ ሀርቨስቲንግ" የተሰኘ በውስጡ ሦስት አገልግሎቶችን የሚሰጥ ዘመናዊ የግብርና ማሽን ፈጥሯል፡፡ ማሽኑ መሬት ማረስ፣ ምርት መሰብሰብ እና ውሃ ፓምፕ ማድረግ የሚችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ይህ ፈጠራ የጊር ቦክስ ስርዓቱን በመቀየር በጋዝ፣ በሶላር እንዲሁም በኤሌክትሪክ ኃይል መስራት የሚያስችል አማራጭ አለው፡፡ ከመሬት ያለው ከፍታ ለየትኛውም የሀገሪቱ የመሬት አቀማመጥ ምቹ እንዲሆን ተደርጎ የተሠራ ነው፡፡ አጠቃላይ የማሽኑ ክብደት 150 ኪሎ ግራም ቢሆንም፣ ሲነቃቀል እያንዳንዱ ክፍል 25 ኪሎ ግራም ብቻ ስለሚመዝን በቀላሉ ተነቃቅሎ እንዲጓጓዝና እንዲገጣጠም አስችሎታል፡፡ ከኢንጂኑ በስተቀር ሁሉም የማሽኑ ክፍሎች በሀገር ውስጥ የተሠራ…

Read the full story at tikvahuniversity ↗
AdYour ad here[email protected]