የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ!
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ! በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ 👇 ከነሐሴ 28/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ የሚያደርጉበት ሊንክ 👇 https://student.ethernet.edu.et/ የሕክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከስድስት ወር በታች ህጻን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል። @tikvahuniversity
Read the full story at tikvahuniversity ↗