ህፃን ልጅ አግታ 4 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡ ወንጀል ፈፃሚዋን በቁጥጥር ለማዋል በተደረው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ ላደረጉ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

BROOK_NEWS_ETHIOPIAneutral2026-09-03 16:54:34 UTC
AdYour ad here[email protected]

ህፃን ልጅ አግታ 4 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡ ወንጀል ፈፃሚዋን በቁጥጥር ለማዋል በተደረው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ ላደረጉ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ መቅደስ ሞገስ የተባለች የቤት ሰራተኛ ከሁለት ወር በፊት የለቀቀችውን የአሰሪዎቿን ቤት በቦሌ ቡልቡላ በመመለስ፣ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ/ም የ7 ዓመቷን ህፃን ፊዮና ሰለሞንን አግታ ተሰወረች፡፡ ወንጀል ፈፃሚዋ ከግብረ አበሯ ጋር በመሆን 4 ሚሊዮን ብር የጠየቀች ሲሆን፣ ቤተሰቦቿ በፍርሃት 370 ሺህ ብር በባንክ ገቢ አድርገውላታል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ባደረገው የቴክኖሎጂና የክትትል ስራ፣ ተጠርጣሪዋ ህፃኗን ይዛ በጎንደር ከተማ ማራኪ ክፍለ ከተማ ዩኒቨርሲቲ ጫካ ውስጥ ተሸሽጋ እያለች በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡

Read the full story at brook_news_ethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]