ማንኛውም አስመጪ ያስገባውን መኪና መሸጥ ያለበት ንግድ ፈቃድ ባወጣበት ቦታ ብቻ ነው።
ማንኛውም አስመጪ ያስገባውን መኪና መሸጥ ያለበት ንግድ ፈቃድ ባወጣበት ቦታ ብቻ ነው። የግብር ስወራ የፈጸሙ 7 የመኪና አስመጪዎች ላይ ዕርምጃ መውሰዱንም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል በመዲናዋ በመኪና አስመጪዎች እና በኮሚሽን ሠራተኞች በኩል የሚፈጸምን የታክስ ስወራ እና የግብር ማጭበርበር ድርጊት ለመግታት ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥራ እየሠራ መሆኑን ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው፣ በርካታ የመኪና አስመጪዎች ለከተማ አስተዳደሩ የሚገባውን ወርሃዊ ቫት እና ዓመታዊ ግብር ላለመክፈል ሲሉ ሽያጮቻቸውን በኮሚሽን ሠራተኞች አማካይነት እያካሄዱ ይገኛሉ። በተጨማሪም አብዛኞቹ አስመጪዎች አድራሻቸው ሳይታወቅ ከዋጋ በታች ደረሰኝ በመቁረጥ ከፍተኛ የግብር ስወራ ወንጀል እንደሚፈጽሙ በተካሄደው ጥናት መረጋገጡ በመግለጫው ተጠቅሷል። በታክስ ሕጉ መሠረት በሌሎች ክልሎች…
Read the full story at addis_reporter ↗