በካፋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
በካፋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል። አደጋው ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ገደማ በወረዳው ቦባ በላ ቀበሌ በተለምዶ ቄነች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መከሰቱ ተገልጿል። በዚህም ኮድ 3-32226 የሆነ ኤፍ ኤስ አር ጭነት መኪና ተገልብጦ በደረሰው አደጋ የአሽከርካሪውና የረዳቱ ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በአደጋው በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ የተገለፀ ሲሆን የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል።አካባቢው ተደጋጋሚ አደጋ የሚደርስበት ሲሆን እና ከፍተኛ ቁልቁለት ያለው ቦታ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት…
Read the full story at zena24now ↗