የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናሚቢያ አዲስ ብሔራዊ አየር መንገድን በሽርክና ለማቋቋም ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር ድርድር ጀመረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናሚቢያ አዲስ ብሔራዊ አየር መንገድን በሽርክና ለማቋቋም ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር ድርድር ጀመረ። የናሚቢያ ሥራና ትራንስፖርት ሚኒስትር ጆናስ ሼሎንጎ እንደገለጹት፤ ውይይቱ ቀደም ሲል "ኤር ናሚቢያ" ላይ ደርሶ የነበረውን የፋይናንስ ውድቀትና መዘጋት ዳግም እንዳይከሰት ለመከላከልና ጠንካራ አየር መንገድ ለመገንባት ያለመ ነው። ሚኒስትሩ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የተደረጉት ውይይቶች ሰፊ የቴክኒክ እና የንግድ ጉዳዮችን ያካተቱ ቢሆንም እስካሁን የተፈረመ አስገዳጅ ስምምነት የለም ብለዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም በቶጎ፣ በማላዊ፣ በዛምቢያ እና በኮንጎ አየር መንገዶች ምሥረታ ላይ አሻራውን ማሳረፉ ይታወሳል ሲል ስፑትኒክ አፍሪካ ። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗