ሰዎችን በማገት የተሳተፉ የወንጀል ቡድን አባላትና የመንግስት ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-04 16:24:49 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሰዎችን በማገት የተሳተፉ የወንጀል ቡድን አባላትና የመንግስት ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋሉ። በባህር ዳር በሰዎች ላይ እገታ በመፈፀም፣ ገንዘብ በመጠየቅና በመቀበል ወንጀል የተሳተፉ የወንጀል ቡድን አባላት እና ለወንጀሉ መፈፀሚያነት የዋለ የመንግሥት ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የባህርዳር ከተማ ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪውቹ ታጋቾቹን አፍነው በመውሰድ ለ11 ቀናት አግተው ያቆዩዋቸው ሲሆን ፤ በወቅቱ ታጋቾቹን ለመልቀቅ 3 ሚሊዮን 370 ሺህ ብር ከቤተሰቦቻቸው በመጠየቅና ገንዘቡ ከተከፈላቸው በኋላ እንዲለቀቁ ማድረጋቸውን የምርመራ መረጃው ያመላክታል። እንደ ፖሊስ መረጃ፣ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 (ኤፍራታ) አካባቢ ነዋሪና ነጋዴ የሆኑ ሶስት ግለሰቦች በራሳቸው ተሽከርካሪ ወደ ስራ ቦታቸው በመሄድ ላይ እያሉ በወቅቱ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]