ያለፍላጎታቸው ሴቶችን በወሲብ ንግድ ላይ ያሰማሩት አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፡፡

ADDIS_REPORTERneutral2026-09-04 16:24:43 UTC
AdYour ad here[email protected]

ያለፍላጎታቸው ሴቶችን በወሲብ ንግድ ላይ ያሰማሩት አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፡፡ በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ አስተዳደር በመጠጥ ግሮሰሪ ንግድ ፈቃድ ሽፋን ሴቶችን ያለ ፍላጎታቸው ለወሲብ ንግድ ሲዳርጉና ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩ አምስት ግለሰቦች እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና የገንዘብ መቀጮ መቀጣታቸውን የከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል። የሮቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ጌታቸው ታምሩ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት፣ ተከሳሾቹ በዘይበላ ወላሼ ቀበሌ «ኤል ክላሲኮ» የተባለ የምሽት ጭፈራ ቤት በመክፈት ሴቶችን በአስተናጋጅነት ካስቀጠሩ በኋላ በግዳጅ ለዝሙት አዳሪነት እንዲሰማሩ አድርገዋል። ፖሊስ ባደረገው ማጣራት አንደኛ ተከሳሽ ተሬሳ ፍቃዱ የንግድ ፈቃዱን በማውጣትና ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በመሆን የተቀጠሩ አስተናጋጆችን…

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]