ሁለቱ የኢሕአፓ ፖለቲከኞች እና ጠበቃ አበራ ንጉሥ በዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ወሰነ!
ሁለቱ የኢሕአፓ ፖለቲከኞች እና ጠበቃ አበራ ንጉሥ በዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ወሰነ! "በሽብር ወንጀል" የተጠረጠሩት ፖለቲከኞቹ አበበ አካሉ እና ይሳቅ ወልዳይ እንዲሁም ጠበቃ አበራ ንጉሥ እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ወሰነ።ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀን ተጨማሪ የምርማራ ጊዜ ቀጠሮ ላይ ትላንት ሐሙስ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም. ክርክር ከተደረገ በኋላ፣ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለዛሬ አርብ 9 ሰዓት ቀጥሮ ነበር። በዚህም መሠረት ጉዳዩን በመከታተል ላይ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፣ የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ እያንዳንዳንዳቸው ተጠርጣሪዎች የ50 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲፈቱ መወሰኑን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጠበቃው እንደገለፁት፣ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት "የመጨረሻ" ያለውን…
Read the full story at addis_news ↗