የጻድቁ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏
የጻድቁ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏 ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም🙏 ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልና አባቱ ካህኑ ቅዱስ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ያገለገለ፤ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፤ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፡፡ ሊቁም ከመላእክት፣ ከነቢያት፣ ከካህናት፣ ከሐዋርያት መካከል እንደርሱ መለኮትን ለማጥመቅ የተመረጠ አለመኖሩን በመጥቀስ “ዮሐንስ ሆይ! ራጉኤል በትጋቱ፣ ኢዮብም በጽድቁ ቢመኙም ሆነ ቢጨነቁ እንደ አንተ የሚነድ እሳት መለኮትን ሊያጠምቁ አልተቻላቸውም” ሲል ታላቅነቱን መስክሮለታል፡፡ ዮሐንስ ማለት እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው፡፡ በሉቃስ 1÷14 እደተጻፈው ወላጆቹ በእርሱ…
Read the full story at addis_news ↗