በሁለት ወራት ዉስጥ ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ነፃ የህክምና አገልግሎት አግኝተዋል ተባለ

ZENA24NOWneutral2026-09-05 10:02:11 UTC
AdYour ad here[email protected]

በሁለት ወራት ዉስጥ ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ነፃ የህክምና አገልግሎት አግኝተዋል ተባለ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ባለፉት ሁለት ወራት ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ማግኘታቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ። የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ እንደተናገሩት በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ለ20 ሚሊዮን ዜጎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አገልግሎቱን አግኝተዋል ። በመርሃ ግብሩ ከተለያዩ የጤና ተቋማትና የጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ዜጎች የሕክምና ምርመራና ሌሎች ነፃ የጤና አገልግሎቶችን ማግኘታቸው ተገልጿል ። በተመሳሳይ መልኩ የደም እጥረትን ለመቀነስ በተደረገው ጥረት 160 ሺህ ዩኒት ደም መሰብሰቡን ዶክተር ደረጄ መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ። በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]