🔥 በአዲስ ከተማ «ሸማ ተራ» ተከስቶ የነበረው
🔥 በአዲስ ከተማ «ሸማ ተራ» ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል 🧑🚒 🔥 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 «ሸማ ተራ» አካባቢ ተከስቶ የነበረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ። የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው እንደገለጹት፤ አደጋውን በፍጥነት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች ትልቅ ትብብር አድርገዋል። 🧑🚒 በአሁኑ ወቅት የአደጋው መንስኤና የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፣ የተደረገው ፈጣን ርብርብ አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ አድርጓል።
Read the full story at brook_news_ethiopia ↗