በአዲስ ከተማ «ሸማ ተራ» ተከስቶ የነበረው
በአዲስ ከተማ «ሸማ ተራ» ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 «ሸማ ተራ» አካባቢ ተከስቶ የነበረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ። የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው እንደገለጹት፤ አደጋውን በፍጥነት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች ትልቅ ትብብር አድርገዋል። በአሁኑ ወቅት የአደጋው መንስኤና የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፣ የተደረገው ፈጣን ርብርብ አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ አድርጓል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗