በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎቿ የምትታወቀው አንጋፋዋ አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-06 11:18:51 UTC
AdYour ad here[email protected]

በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎቿ የምትታወቀው አንጋፋዋ አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የኦሮሚያ ክልል " አርቲስት እልፍነሽ ለበርካታ ዓመታት በተለይም በትግል ዘፈኖቿና በግጥሞቿ ለኦሮሞ ሕዝብ መብት ስትታገል ቆይታለች " ብሏል። " አርቲስቷ የጥበብን ኃይል በመጠቀም በሕዝባዊ ትግል ውስጥ ከፍተኛ ሚና በመጫወት በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ድምጻውያን መካከል ናት " ሲል ገልጿል። በምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ሲቡ ጉቶ በተባለች ስፍራ የተወለደችው እልፍነሽ በ1969 ወደ ትግል በመቀላቀል ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሥነ-ጥበብ ሥራዎቿ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክታለች። ለበርካታ ዓመታት ከኖረችበት ኖርዌይ በቅርቡ ወደ ሀገሯ የተመለሰች ሲሆን፤ ባደረባት ሕመም በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡ ጳጉሜን 1 ቀን…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]