የበዓል ዝግጅት
የበዓል ዝግጅት የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ሥራ ኮሚሽን ለመጪዎቹ የአዲስ ዓመት፣ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት የምርት አቅርቦት እንዳይጎድል ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ሽታዬ ሙሐመድ እንዳስታወቁት፣ ለበዓላቱ የሚያስፈልጉ ጤፍ፣ ነጭ ዱቄት፣ ዘይት፣ እንቁላል፣ ዶሮና ሌሎች መሠረታዊ ምርቶች በበቂ ሁኔታ እንዲቀርቡ ከዩኒየኖች፣ ከሸማች ማህበራትና ከአምራች አካላት ጋር ሥራ እየተሰራ ነው። በተለይ የሽንኩርት አቅርቦትን በተመለከተ፣ ከክልሎች ካሉ ዩኒየኖች ጋር ትስስር በመፍጠር ምርቱን ወደ አዲስ አበባ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ኮሚሽነሯ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም በሸማች ማህበራት የሚቀርበው ሽንኩርት ከ60 እስከ 65 ብር አካባቢ እንደሚሸጥ ጠቁመዋል። ሽንኩርት ላይ በክረምት ወቅት የዋጋ ጭማሪ፣ በበጋ ደግሞ የዋጋ ቅናሽ የመኖር ዝንባሌ እንዳለ የገለጹት…
Read the full story at tikvahethiopia ↗