💔በግብፅ ቴሌቭዥን "ሚሽን ኢምፖሲብል" የተሰኘው ታዋቂ የወንጀል ምርመራ ፕሮግራም የቀድሞ አቅራቢ የ39 ዓመቷ ሣራ ኸሊፋ የሞት ፍርድ ተላለፈባት።

BROOK_NEWS_ETHIOPIAneutral2026-09-06 18:02:37 UTC
AdYour ad here[email protected]

💔በግብፅ ቴሌቭዥን "ሚሽን ኢምፖሲብል" የተሰኘው ታዋቂ የወንጀል ምርመራ ፕሮግራም የቀድሞ አቅራቢ የ39 ዓመቷ ሣራ ኸሊፋ የሞት ፍርድ ተላለፈባት። ሣራ ኸሊፋ ዛሬ የካይሮ ፍርድ ቤት በከፍተኛ አደገኛ ዕፆች ዝውውር መረብ ውስጥ በነበራት ተሳትፎ ጥፋተኛ ብሎ የሞት ፍርድ ሲበይንባት በዕንባ መንሰቅሰቋ ታውቋል። በማህበራዊ ሚዲያ ከ2 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሏት ሣራ ኸሊፋ ለፍርድ ቤቱ ዳኞች "እባክዎን ያዳምጡኝ ጌታዬ፤ ወላጆቼ በስርዓት ነው ያደጉኝ፤ ሶላት የሚሰግዱ አማኞች ናቸው፤ እኔ ደግሞ የዕፅ ገንዘብ አያስፈልገኝም" በማለት ብትማፀንም ሰሚ አላገኘችም። ሳራ ከቴሌቪዥን አቅራቢነቷ በተጨማሪ የራሷን የፕላስቲክ ሰርጀሪ ክሊኒክ እና የቴሌቭዥን ዝግጅት ማስተባበር ኩባንያ እንደምታስተዳድር ታውቋል። #NewYorkPost

Read the full story at brook_news_ethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]