ከማረሚያ ቤት ከተፈታ በሦስተኛ ቀኑ የአምቡላንስ ተሽከርካሪ ቁልፍ የሰረቀው ግለሰብ በጽኑ እሥራት ተቀጣ።
ከማረሚያ ቤት ከተፈታ በሦስተኛ ቀኑ የአምቡላንስ ተሽከርካሪ ቁልፍ የሰረቀው ግለሰብ በጽኑ እሥራት ተቀጣ። ከዚህ ቀደም በተጣለበት የፍርድ ውሳኔ መሠረት በማረሚያ ቤት ቆይታ የእስር ጊዜውን አጠናቆ በወጣ በሦስተኛው ቀን በድጋሚ በስርቆት ወንጀል የተከሰሰው አቶ ያሬድ ገብረሚካኤል የተባለው ግለሰብ መሆኑ የአክሱም ከተማ ፖሊስ አስታውቋል። የማዕከላዊ ዞን ዓቃቤ ሕግ ቢሮ እንዳስታወቀው ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ያለችን እህቱን ለመጠየቅ የመጓጓዣ ገንዘብ እንደሌለው በመግለጽ በዓድዋ ከተማ ቀይ መስቀል ማህበር አምቡላንስ ተሳፍሮ በመጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት ነው። ግለሰቡ በተሳፈረበት አምቡላንስ ውስጥ ተቀምጦ የነበረውን የተሽከርካሪውን ቁልፍ ሰርቆ ከተሰወረ በኋላ በጸጥታ አካላት በተደረገ ክትትል በአክሱም…
Read the full story at addis_reporter ↗