ለአዲስ አመት ከ4 ሺህ በላይ የእርድ እንስሳትን እንደሚያቀርብ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታወቀ

ZENA24NOWneutral2026-09-07 12:29:01 UTC
AdYour ad here[email protected]

ለአዲስ አመት ከ4 ሺህ በላይ የእርድ እንስሳትን እንደሚያቀርብ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታወቀ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የዘንድሮውን የአዲስ አመት በዓል አስመልክቶ በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥቷል። የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮማንደር አህመድ መሀመድ ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት ተቋሙ በመጪው የአዲስ ዓመት በዓል 4 ሺህ 500 የቁም የእንስሳትን እርድ ለማከናወን ዝግጅት አጠናቋል። ከእነዚህም መካከል ከ3 ሺህ በላይ በሬዎች እና ከ1 ሺህ 500 በላይ በግና ፍየሎች እርድ እንደሚከናወን ተገልጿል። የከተማዋ ነዋሪዎችም በግና ፍየልን በ300 ብር፣ እንዲሁም በሬዎችን ደግሞ በ2ሺ 100 ብር የቄራ የእርድ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የተጠቀሰው። ሕብረተሰቡ ጥራታቸውና ደህንነታቸው የተጠበቁ ሥጋዎችን እንዲያገኝ ወደ ቄራዎች…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]