በቦንጋ ከተማ የተሰረቁ ሞባይሎችን የገዙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በቦንጋ ከተማ የተሰረቁ ሞባይሎችን የገዙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ . በቦንጋ ከተማ የተሰረቁ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በተለይም ሞባይሎችን የገዙና የተቀበሉ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የቦንጋ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል። የቦንጋ ከተማ ወጣቶች ያለአግባብ እየታሰሩ ነው በሚል በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑንና ዓላማውም ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች በህግ እንዳይጠየቁ ለማድረግ እንደሆነ ፖሊስ ገልጿል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት በከተማው የስርቆት ወንጀል ተፈጽሞ የተሰረቁ ሞባይሎችን የሚገዙ፣ የሞባይል ይለፍ ቃል የሚጠልፉ እና ከህገወጥ የስርቆት ተግባር ፈጻሚዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው አምስት ግለሰቦች በመረጃ እንዲለዮ ተደርጓል።…
Read the full story at zena24now ↗