#እንድታውቁት
#እንድታውቁት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለኢ-ፓስፖርት ማመልከት የሚፈልጉ ዜጎች ከሐሰተኛ ድረ-ገጾች እንዲጠነቀቁ አሳስቧል። አገልግሎቱ እንዳስታወቀው አንዳንድ አጭበርባሪዎች የኤምባሲዎችን ገጽ በመምሰል ሐሰተኛ የኢ-ፓስፖርት ማመልከቻ ፖርታሎችን እያሰራጩ ነው። ይህም አመልካቾችን ለተጨማሪ ወጪና እንግልት ሊዳርግ እንደሚችል አገልግሎቱ ገልጿል። በመሆኑም ለኢ-ፓስፖርት ማመልከት የሚፈልጉ ዜጎች https://immigration.gov.et/?fbclid የሚለውን ይፋዊ ድረ-ገጽ ብቻ እንዲጠቀሙ አሳስቧል። @TikvahethMagazine
Read the full story at tikvahethmagazine ↗