ትራምፕ ካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ ግሪንላንድ፣ አይስላንድ እና ሌሎችንም ግዛቶች ከአሜሪካ ጋር አቀላቅሎ የሚያሳይ ካርታ አጋሩ፡፡
ትራምፕ ካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ ግሪንላንድ፣ አይስላንድ እና ሌሎችንም ግዛቶች ከአሜሪካ ጋር አቀላቅሎ የሚያሳይ ካርታ አጋሩ፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን አሜሪካን እና አቅራቢያ የሚገኙ ግዛቶችን በአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ስር አጠቃሎ የሚያሳይ ካርታ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ አጋርተዋል። ይህም አዘጋጅተው ያቀረቧቸውን ካርታዎች እና የጂኦግራፊያዊ ስሞች ለውጦችን ለፖለቲካዊ መልእክት ማስተላለፊያነት የመጠቀም አካሄዳቸው መቀጠሉን ያሳያል።ያለ ምንም ተጨማሪ ማብራሪያ የተለቀቀው ይህ ምስል፤ አሜሪካን ጨምሮ ሰፊውን የካናዳ፣ የግሪንላንድ እና የሜክሲኮ ግዛቶች በአሜሪካ ባንዲራ ተሸፍነው ያሳያል። አርክቲክ ቱደይ እንዳስነበበው፤ ይህ ምስል ማዕከላዊ አሜሪካን፣ ካሪቢያንን እና አይስላንድን ያካተተ ሲሆን፤ መላው ቀጠናም የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ መንግስት በሚል ተሰይሟል። በምስሉ…
Read the full story at addis_news ↗