"ነገ በካሜራ መጥቼ እንዳላቀጣህ አሁኑኑ ገንዘብ አምጣ እየተባልን ነው" ነጋዴዎች
"ነገ በካሜራ መጥቼ እንዳላቀጣህ አሁኑኑ ገንዘብ አምጣ እየተባልን ነው" ነጋዴዎች በገቢዎች ባለስልጣን ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ላይ የተገጠመው የሰውነት ካሜራ (Body Camera) ሙስናንና ሌብነትን ለማስቀረት ያለመ ቢሆንም፣ በተግባር ግን የስርቆት ስልቱን ከመቀየር ባለፈ ያገደው ነገር የለም ሲሉ ነጋዴዎች አሰሙ። ነጋዴዎች ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ተቆጣጣሪዎቹ ከስራ ሰዓት ውጭ ዩኒፎርምና ካሜራቸውን አውልቀው በመመለስ "ነገ በካሜራ መጥቼ እንዳላቀጣህ አሁኑኑ ገንዘብ አምጣ" በማለት ማስፈራራትን እንደ አዲስ ስልት ይዘውታል። ከዚህ በተጨማሪም፦ 📌 በየሆቴሉና ሬስቶራንቱ በመግባት ተመግበው ክፍያ እንደማይከፍሉና ክፍያ የጠየቃቸውን ባለቤት በሰበብ አስባቡ እንደሚያስፈራሩ፤ 📌 ገዢ የሚመስል የራሳቸውን ሰው ወደ ሱቅ በመላክ ደረሰኝ ሳይቀበል እንዲወጣ ካደረጉ በኋላ "እጅ ከፊንጅ ተያዛችሁ"…
Read the full story at wasulife ↗