በደቡባዊ ሳዑዲ አረቢያ በሁቲዎች በተፈጸመ ጥቃት 73 ሲቪሎች ቆሰሉ

ADDIS_NEWSneutral2026-09-09 09:49:35 UTC
AdYour ad here[email protected]

በደቡባዊ ሳዑዲ አረቢያ በሁቲዎች በተፈጸመ ጥቃት 73 ሲቪሎች ቆሰሉ የየመኑ ሁቲ አማፂ በደቡባዊ ሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ከተሞችና የኢኮኖሚ መሰረተ ልማቶች ላይ በሰነዘረዉ ጥቃት ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 73 ሲቪሎች መቁሰላቸውን በሳዑዲ መሪነት የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ወታደራዊ ጥምረት አስታዉቋል። የጥምረት ኃይሉ ቃል አቀባይ ሜጀር ጄነራል ቱርኪ አል-ማሊኪ በሰጡት መግለጫ፤ የሁቲ ታጣቂዎች በአብሃ፣ ኻሚስ ሙሻይት፣ ጃዛን እና ናጅራን ከተሞች በሚገኙ የሲቪልና የንግድ ተቋማት ላይ ‹‹ትርጉም የለሽ እና አደገኛ ጥቃቶችን›› መፈጸማቸውን ገልፀዋል። በጥቃቱ ሳቢያ በህዝብና በንግድ ተቋማት ላይ ከፍተኛ የንብረት ውድመት የደረሰ ሲሆን፤ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ የማረጋጋት እና የደህንነት ቁጥጥር የማጠናከር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]