"እርቅ ተፈጸመ ሲባል በማግስቱ ሁለት፣ ሦስት ሰዎች ይገደላሉ" - የክልሉ ምክር ቤት አባል

ADDIS_REPORTERneutral2026-09-09 16:24:02 UTC
AdYour ad here[email protected]

"እርቅ ተፈጸመ ሲባል በማግስቱ ሁለት፣ ሦስት ሰዎች ይገደላሉ" - የክልሉ ምክር ቤት አባል በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት በሚደርስበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጥቃቱ ባለመቆሙ ሰሞኑንም ንጹሐን መገደላቸውን፣ ንብረት መዘረፉን አንድ የዞኑ አመራርና የክልሉ ምክር ቤት አባል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። አመራሩ በሰጡን ቃል፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላናና ሱሮባርጉዳ ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸሙ መሆናቸውን አስረድተዋል። መላኩ ማዝሬ የተባሉ ግለሰብ ከብቶች በማሰማራት ላይ በነበሩበት ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጸዋል። ከምዕራብ ጉጂ ዞን ከጋላና ወረዳ ወደ ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ቆቦ ቀበሌ ዘልቀው በገቡ የጉጂ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ግለሰቡ መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ማረጋገጣቸውንም…

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]