በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጌዴኦ ዞን፣ ዲላ ከተማ ጪጩ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አቢቲ ብርሃኑ የተባለ ወጣት በፌዴራል ፖሊስ አባል በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጌዴኦ ዞን፣ ዲላ ከተማ ጪጩ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አቢቲ ብርሃኑ የተባለ ወጣት በፌዴራል ፖሊስ አባል በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። ወጣቱ ገና ከተሞሸረ 3 ወር ብቻ እንደሆነው ጠቁመዋል። አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የጪጩ አካባቢ ነዋሪ እንደገለጹት፣ ግድያው የተፈጸመው ትናንት በፌዴራል ጉምሩክ ኬላ ከሚገኘው አካባቢ በግምት ሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወጣቱ እየተዝናና ባለበት ወቅት ነው። የወጣቱ ሕይወት ያለፈው የፌዴራል ፖሊስ አባል በተኮሰበት ጥይት መሆኑንም ምንጩ ገልጸዋል። የግድያው ምክንያት በግልጽ የታወቀ ነገር እንደሌለ የገለጹት ምንጩ፣ "በኮንትሮባንድ ምክንያት ነው" ሲባል መስማታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። የወጣቱ ሕይወት ማለፉ በአካባቢው ከተሰማ በኋላ ለሰዓታት አለመረጋጋት…
Read the full story at tikvahethiopia ↗