መልካም አዲስ ዓመት ! 🎉🇪🇹

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-10 20:59:37 UTC
AdYour ad here[email protected]

መልካም አዲስ ዓመት ! 🎉🇪🇹 አዲሱ ዓመት 2019 የሰላም ዜና የምንሰማበት ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ድምፅ የሚሰማበት ፤ የሀዘን እንባ በደስታ እንባ የሚተካበት ፣ ቤተሰቦች በሰላም የሚገናኙበት ፣ ወጣቶች በተስፋ ወደ ግባቸው የሚመለከቱበት ግባቸውን የሚያሳኩበት ዓመት ይሁንልን። ግጭት ቦታውን ለሰላም፣ ፍርሃት ለተስፋ፣ ችግር ለመፍትሔ የሚለቅበት፤ የኑሮ ጫና የሚቀልበት፣ ሠርቶ መለወጥ የሚቻልበት፣ በሀገራችን መኖር ኩራት የሚሆንበት ስኬትን የሚያጎናፅፍበት ልዩ ዓመት ይሁንልን። ለውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ፤ 2019 ዓ/ም የጤና፣ የስኬት፣ የበረከትና የሰላም ዓመት ይሁንላችሁ። ያሰባችሁት ይሳካ፣ የምትወዷቸው ሁሉ በሰላም አይኖቻችሁን ይመልከቱ ፤ በየቀኑም ለመደሰት አዲስ ምክንያት ይኑራችሁ። ፈጣሪ ለሀገራችን ሰላምን፣ ለህዝባችን ተስፋን፣ ለእያንዳንዳችንም ጤናና በረከትን ይስጠን…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]