የአምስቱ ጋዜጠኞች ውሳኔ እና የሲፒጄ ጥሪ‼

ADDIS_NEWSneutral2026-09-12 06:01:25 UTC
AdYour ad here[email protected]

የአምስቱ ጋዜጠኞች ውሳኔ እና የሲፒጄ ጥሪ‼ በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ምንም አይነት ወንጀል ስላልፈጸሙ ይቅርታ ጠይቀው ከእስር እንዲፈቱ የቀረበላቸውን ሀሳብ አለመቀበላቸውን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ወይም ሲፒጄ አስታውቋል። ጋዜጠኞቹ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና አባይ ዘውዱ ሲሆኑ በአማራ ክልል ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2023 የተያዙ ናቸው። ከዚያም በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰሰው የፍርድ ቤት ሂደታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል። የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ እንደገለጹት የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ጋዜጠኞቹን ከሌሎች ታሳሪዎች በመለየትና በማስፈራራት መንግስት ያዘጋጀውን የይቅርታ ወረቀት ፈርመው ከእስር እንዲወጡ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ስራቸውን እንዲተዉ ጫና ሲያደርጉባቸው ነበር።…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]