ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን እያተራመሰች ነው ስትል ኤርትራ ከሰሰች።

ADDIS_NEWSneutral2026-09-12 11:32:38 UTC
AdYour ad here[email protected]

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን እያተራመሰች ነው ስትል ኤርትራ ከሰሰች። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው «የኢትዮጵያው ገዢ የብልጽግና ፓርቲ የአፍሪካ ቀንድን አለመረጋጋት ውስጥ ለመዝፈቅ በንቃት እየሰራ ነው» ሲል ከሷል። «ኢትዮጵያ በማያቋርጥ ሁኔታ በኤርትራ ላይ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመች ነው» ያለው መግለጫው ኤርትራ ግን በስትራተጂያዊ ትዕግስቷ ጸንታለች» ብሏል።በተጨማሪም ኢትዮጵያ «ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በመጣስ በኤርትራ ላይ ግልጽ የሆነ የሥርዓት ለውጥ አጀንዳ የያዙ ቅጥረኛ ቡድኖችን በማስተናገድ፣ በማሰልጠንና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ተጠምዳለች» ሲልም አክሏል መግለጫው። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ስለኤርትራው ክስ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅሕፈት ቤት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካለት…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]