#ወልዋሎ

ZENA24NOWneutral2026-09-12 15:25:44 UTC
AdYour ad here[email protected]

#ወልዋሎ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወደ ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ አለፈ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታውን ሲያካሂድ የቆየው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ የሱዳኑን ሂላል አል-ሳሂል በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል። በመልሱ ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተፎካካሪውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ የቻለ ሲሆን፣ በሁለቱ ጨዋታዎች በድምር ውጤት 3 ለ 3 መጠናቀቁን ተከተሎ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ መለያ ምት ወልዋሎ 4 ለ 1 በሆነ በላቀ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከዛንዚባሩ 'ኬኤምኬኤም' (KMKM) እና ከሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ ጨዋታ አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል። #ዳጉ_ጆርናል

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]