በጋምቢያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለ 48 ሰዓታት በመቋረጡ ዜጎች ከፖሊሶች ጋር ግጭት ዉስጥ ገቡ
በጋምቢያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለ 48 ሰዓታት በመቋረጡ ዜጎች ከፖሊሶች ጋር ግጭት ዉስጥ ገቡ ጋምቢያ ባጋጠማት ሀገራዊ የኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥ የተነሳ ነዉጥ ላይ ነች ተብሏል። ላለፉት ከ 16 - 48 ሰዓታት ሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ሀይል ተቋርጦባት ቆይቷል። ይህ ያላስደሰታቸው ዜጎቿም ከፍተኛ ተቃዉሞ እና ነዉጥ አስነስተዉ ከፖሊስ ጋር ግጭት ዉስጥ ገብተዋል ተብሏል። 75 በመቶ የኤሌክትሪክ ፍጆታዋን ከሴኔጋል የምታገኘዉ ጋምቢያ ስራዎች መቆማቸዉ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ ሞቃታማ በመሆኗ ነዋሪዎቿ የአየር ማቀዝቀዣ (AC) ስርዓታቸው መቋረጡ ለተቃዉሞዉ ምክኒያት ነዉ ተብሏል። ፖሊስ በአስለቃሽ ጭስ ተቃዋሚዎችን እየበተነ ሲሆን ማናቸዉንም ስብሰባዎች እና በምሽት በብዛት የሚደረጉ ድርጊቶችን አግዷል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗