🇪🇹የኢትዮጵያ መንግሥት በቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት ያጋጠመውን የደህንነት ስጋት ለመቅረፍ እጥራለሁ አለ❗️
🇪🇹የኢትዮጵያ መንግሥት በቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት ያጋጠመውን የደህንነት ስጋት ለመቅረፍ እጥራለሁ አለ❗️ 💎 በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ በቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት ያጋጠመውን የደህንነት አደጋ ተከትሎ በሠራተኞች ላይ ተጨማሪ ጉዳት አለመድረሱን የከፊ ጎልድ ኤንድ ኮፐር ኩባንያ ገልጿል። የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትና የልማት ሥራዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ለመቀጠል ከአካባቢው፣ ከፌደራልና ከክልል መንግሥት አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል። 🇪🇹 መንግስት ይህን ተግዳሮት ለመወጣት የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገብቷል። 💎 ኩባንያው ሙሉ ምርመራ እስኪያጠናቅቅ እና ለሠራተኞቹ እንዲሁም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ የሥራ ካባቢ ለመፍጠር የሚያስችሉ ተገቢ እርምጃዎች እስኪወሰዱ ድረስ እንቅስቃሴዎቹን እንደማይጀምር ይፋ አድርጓል።
Read the full story at brook_news_ethiopia ↗