🇪🇹ማሌዥያ፤ ኢትዮጵያ በኳላላምፑር ኤምባሲዋን እንድትከፍት ጥሪ አቀረበች
🇪🇹ማሌዥያ፤ ኢትዮጵያ በኳላላምፑር ኤምባሲዋን እንድትከፍት ጥሪ አቀረበች የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ከ18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከኢትዮጵያ አቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው ጥያቄውን ያቀረቡት። ሁለቱ መሪዎች በተጨማሪም በሚቀጥለው ዓመት በኳላላምፑር የመጀመሪያውን የሁለትዮሽ የምክክር መድረክ ለማካሄድ ተስማምተዋል። ማሌዥያ ከ43 ዓመታት ቆይታ በኋላ በመስከረም 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤምባሲዋን ዳግም መክፈቷ ይታወሳል።
Read the full story at brook_news_ethiopia ↗