"ከእስር መፈታት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሉባልታዎች መሠረተ-ቢስ ናቸው" - አቶ ክርስቲያን ታደለ

ADDIS_NEWSneutral2026-09-13 13:46:37 UTC
AdYour ad here[email protected]

"ከእስር መፈታት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሉባልታዎች መሠረተ-ቢስ ናቸው" - አቶ ክርስቲያን ታደለ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ከእስር የተፈቱት አቶ ክርስቲያን ታደሰ በእስር ቆይታቸው ከእሳቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጎን ለቆሙ ግለሰቦችና ተቋማት ምስጋና አቀረቡ። አቶ ክርስቲያን በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰራጩት የምስጋና መልዕክት፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከእሳቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጎን ለቆሙ ሁሉ ልባዊ ምስጋናቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪ አሁን ላይ የጤናቸውን ሁኔታ እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸው " ከእስር መፈታት ጋር ተያይዞ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሉባልታዎች መሠረተ-ቢስ " መሆናቸውን አስታውቀዋል። የጤናቸው ሁኔታ ሲሻሻል በጉዳዩ ዙሪያ ያለውን እውነታ በዝርዝር ለሕዝብ እንደሚያሳውቁ አቶ ክርስቲያን ታደለ ገልጸዋል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]