"አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ከ600 በላይ እስረኞች የተፈቱት ራሳቸው ባቀረቡት ጥያቄ ነው"ኢሰመኮ

WASULIFEneutral2026-09-14 13:09:24 UTC
AdYour ad here[email protected]

"አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ከ600 በላይ እስረኞች የተፈቱት ራሳቸው ባቀረቡት ጥያቄ ነው"ኢሰመኮ ​የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከእስር የተፈቱት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ዶ/ር ጫኔ ከበደ እና ዶ/ር ካሳ ተሻገርን ጨምሮ ከ600 በላይ ታራሚዎች ነፃ የወጡት ራሳቸው በኮሚሽኑ በኩል ባቀረቡት ጥያቄ መሆኑን ገለጸ። ​📌 ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ እንደገለጹት፤ እስረኞቹ በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ የክስ ማቋረጥ ውሳኔን በፊርማ ጠይቀው የተለቀቁ ናቸው። 📌 በተመሳሳይ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ውስጥ 28 ሰዎች የይቅርታ ጥያቄ ባለማቅረባቸው ጉዳያቸው እንዳልታየ ተገልጿል። 📌 በፌዴራል ደረጃ ከተፈቱት በተጨማሪ በአማራ ክልል 70፣ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ከ250 በላይ እስረኞች በዚሁ ልዩ ሁኔታ ተፈትተዋል።…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]