የዓለም ንግድ አዲስ ስጋት፡ ሁቲዎች ሁለት ተጨማሪ ስትራቴጂካዊ ደሴቶችን ተቆጣጠሩ
የዓለም ንግድ አዲስ ስጋት፡ ሁቲዎች ሁለት ተጨማሪ ስትራቴጂካዊ ደሴቶችን ተቆጣጠሩ የየመን ሁቲ አማጺያን በደቡባዊ ቀይ ባሕር የሚገኙትን ሁለት ስትራቴጂካዊ ደሴቶች መቆጣጠራቸውን ይፋ አደረጉ። ይህ እርምጃ በዓለም አቀፍ የባሕር ንግድ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። አማጺያኑ በባቢል መንደብ አቅራቢያ የሚገኙትን ቬሊኪ ሀኒሽ እና ማሊ ሀኒሽ ደሴቶችን የተቆጣጠሩት የመንግሥት ኃይሎች ከአካባቢው ማፈግፈጋቸውን ተከተሎ ነው። ሁቲዎቹ ከቀናት በፊት የሞካ ወደብን እና የመጁን ደሴትን መያዛቸው ይታወሳል። ይህ ግስጋሴ በየመን እንደገና አጠቃላይ የእርስ በርስ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። የቀይ ባሕር መስመር ለዓለም አቀፍ የነዳጅና የእቃ ማጓጓዣ ቁልፍ በመሆኑ፣ የደህንነት መዛባቱ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ተብሎ ይጠበቃል። @Addis_News…
Read the full story at addis_news ↗