መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ወታደር አስወጥቻለሁ - ተማሪዎችን እቀበላለሁ ብሏል‼
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ወታደር አስወጥቻለሁ - ተማሪዎችን እቀበላለሁ ብሏል‼ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ፣ የኩሓ መለስ ቴክኖሎጂ ካምፓስ በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች መልሶ ማቋቋሚያ እና ለተዋጊዎች ትጥቅ መፍታት (DDR) ፕሮግራም አገልግሎት ሲውል በመቆየቱ ላለፉት አምስት ዓመታት ለመማር ማስተማር አገልግሎት እንዳልዋለ አስታውቋል። ዩኒቨርሲቲው ካምፓሱን ሙሉ በሙሉ አስለቅቆ ወደ ነባር ይዞታው ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እያደረገ መሆኑን ገልጾ፣ ትምህርት ሚኒስቴር ባሉት ሌሎች 6 ካምፓሶች ያለውን የመቀበል አቅም እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የተመደቡለትን ተማሪዎች እንዲልካለት ጠይቋል። ዛሬ ት/ሚንስቴር በትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እንደሚመድብ ማስታወቁ ይታወሳል።…
Read the full story at wasulife ↗