ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ለትልቁ ህልሟ ስትል

ADDIS_NEWSneutral2026-09-15 10:33:34 UTC
AdYour ad here[email protected]

ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ለትልቁ ህልሟ ስትል መኖሪያ ቤቷን በባንክ ማስያዟን ገለጸች ታዋቂዋ ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ በአዲስ አበባ ከተማ ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት የማዘጋጀት ህልሟን ለማሳካት መኖሪያ ቤቷን በባንክ ማስያዟን በማህበራዊ ገጿ አስታወቀች። ላለፉት ሦስት ዓመታት በሀገር ውስጥ ኮንሰርቶችም ሆነ ክለቦች ውስጥ ሳትታይ የቆየችው ድምጻዊቷ፣ ከ20 በላይ ከሚሆኑ ፕሮሞተሮች ጋር ብታወራም የኮንሰርቱ ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ አብረዋት ለመስራት ሳይችሉ መቅረታቸውን ገልጻለች። በዚህም ምክንያት ህልሟን እውን ማድረግ የምትችለው ራሷ ብቻ መሆኑን በመረዳት «መጠሪያዬ ቱር» የተሰኘውን ታላቅ ኮንሰርት በራሷ ወጪ ለማዘጋጀት ወስና ቤቷን በባንክ አስይዛለች። ከአዲሱ አልበሟ ዝግጅት ጋር ተያይዞ ሀብቷ ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ በመዋሉ ይህን ውሳኔ ማሳለፏን የገለጸች ሲሆን፣ ለዚህ ስኬትም ከቡድኗ ጋር…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]