ሁቲዎች ስትራቴጂካዊ የሆኑትን የቀይ ባህር ደሴቶች ተቆጣጠሩ

ADDIS_NEWSneutral2026-09-15 12:14:00 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሁቲዎች ስትራቴጂካዊ የሆኑትን የቀይ ባህር ደሴቶች ተቆጣጠሩ ተንታኞች የነዳጅ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦት ቀውስ እንደ አዲስ ሊያገረሽ ይችላል የሚሉ ስጋቶች በጨመሩበት ወቅት፣ በኢራን የሚደገፈውና በየመን የሚንቀሳቀሰው የሁቲ አማፂ ቡድን ቁልፍ የሆነውን የባህር ንግድ መስመር የመቆጣጠር አቅሙን የሚያጠናክሩ ሁለት ስትራቴጂካዊ የቀይ ባህር ደሴቶችን በእጁ አስገብቷል። አማፂው ቡድን በባብ ኤል-መንደብ ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙትን ታላቁ እና ታናሹ ሐኒሽ ተብለው የሚጠሩትን ደሴቶችን ተቆጣጥሯል። የአማጺው አባላት እነዚህን ደሴቶች መቆጣጠራቸው፣ ቡድኑ በባብ ኤል-መንደብ ወሽመጥ የሚገኘውን የሞካ ወደብ እና የፔሪም ደሴትን ከተቆጣጠረ በኋላ በየመን የቀይ ባህር ዳርቻ ያከናወነው ፈጣን ግስጋሴ አካል ነው ተብሏል። የሁቲዎችን የፈጣን ግስጋሴ…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]