" ሁለት ሰላማዊ ወጣቶች ተገድለዋል " - የኮሬ ዞን ነዋሪዎች
" ሁለት ሰላማዊ ወጣቶች ተገድለዋል " - የኮሬ ዞን ነዋሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ጎልቤ ቀበሌ ሁለት ሰላማዊ ወጣቶች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፣ ከምዕራብ ጉጂ በኩል የመጡ ታጣቂዎች ወደ ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ጎልቤ ቀበሌ በመግባት፣ በሞተር ሳይክል ወደ ኬሌ ከተማ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ወጣቶችን ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ በጥይት ገድለዋል። ጥቃቱ ቡርጂ ዞንን ከኮሬ ዞን በሚያገናኘው ዋናና ብቸኛ መንገድ፣ በጎልቤ ቀበሌ "ቦኮሶ" በሚባል የዳኖ እና ጎልቤ ቀበሌዎች አዋሳኝ ቦታ መፈጸሙንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የአካባቢው አመራር፣ " መንግስት ባለበት ሀገር በፓርላማ ቢጮህ፣ በየስብሰባው ለዘመናት አልቅሰን ብሶታችንን ብንገልፅ የሚሰማንን አልተገኘም " ብለዋል። " አሁን ላይ በምዕራብ ጉጂ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗