በአማራ ክልል በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ባለፉት ሦስት ዓመታት ከትምህርት ውጭ የነበሩትን ህጻናት በበቂ ሁኔታ ተቀብለው ለማስተማር የሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ አይገኙም ተባለ።
በአማራ ክልል በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ባለፉት ሦስት ዓመታት ከትምህርት ውጭ የነበሩትን ህጻናት በበቂ ሁኔታ ተቀብለው ለማስተማር የሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ አይገኙም ተባለ። የአማራ ክልል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት (ARCSOC) በክልሉ ያለውን የትምህርት ሁኔታ በሚመለከት መግለጫ አውጥቷል። ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በደረሰው በእዚህ መግለጫ ምክር ቤቱ ጥራት ያለው ትምህርት በእኩልነት የማግኘት መብት የሰብዓዊ መብትና የማህበራዊ ፍትህ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሶ፣ በአማራ ክልል ባለፉት 3 ዓመታት በተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ዘርፉ በተለያዩ መልኩ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን አመልክቷል። ተቋሙ ባለፉት ሦስት አመታት በግጭት ውስጥ በቆየው አማራ ክልል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው እንዲገለሉ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን…
Read the full story at tikvahethiopia ↗