70 በመቶ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ እንዲመደቡ ተደረገ።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-09-16 20:55:58 UTC
AdYour ad here[email protected]

70 በመቶ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ እንዲመደቡ ተደረገ። የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ የተደረገ ሲሆን አንዱ ታሳቢ የተደረገው የተማሪዎች የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የትምህርት ቤት ስርጭት መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። በዚህም 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ 30 በመቶዎቹ ደግሞ በተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውስጥ ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በተጨማሪ የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጎ መመደቡንም ገልጿል። ምደባ ለማየት ፦ https://student.ethernet.edu.et/view-placement ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]