በሱዳን የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ ከ80 በላይ ሰዎች ሞቱ። በርካቶች ፍርስራሽ ስር ይገኛሉ።
በሱዳን የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ ከ80 በላይ ሰዎች ሞቱ። በርካቶች ፍርስራሽ ስር ይገኛሉ። በሱዳን ምዕራብ ኮርዶፋን ግዛት የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ 82 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን እና በርካቶች መቁሰላቸውን፣ ቁጥራቸው ያልታወቀ የማዕድን አውጪዎች በፍርስራሹ ሥር ተቀብረው እንደሚገኙ ተዘግቧል። አደጋው የተከሰተው "አል-ዛራ" በተሰኘው የወርቅ ማዕድን ማውጫ ቦታ ላይ ነው። እስከ ረቡዕ ጠዋት ድረስ የ60 ሰዎች አስከሬን፣ ከዚያ በኋላ ላይ ደግሞ የሌሎች 22 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። ምዕራብ ኮርዶፋንን በቁጥጥሩ ሥር ያደረገው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) አባል የሆኑ አንድ የአካባቢው አስተዳዳሪ እንደገለጹት፣ ወደ 50 የሚጠጉ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች አሁንም በፍርስራሹ ስር ይገኛሉ።(ThiqahEth) #WasuMohammed እዚህ ድምፅ ይስጡ👇…
Read the full story at wasulife ↗