በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደቡ እንዲሁም ለነባር ተማሪዎች በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይገለጻል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር
በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደቡ እንዲሁም ለነባር ተማሪዎች በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይገለጻል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በጠየቁት መሠረት፣ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እስኪስተካከል ድረስ በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንድትመደቡ የሚደረግ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡ "በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል መሔድ ሳይጠበቅባችሁ፣ የትምህርት ሒደታችሁ እንዳይስተጓጎል እና ደኅንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን በመደበኛነት እንድትቀጥሉ ለማስቻል በጊዜያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ" ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ "ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲስተካከል፣ መጀመሪያ በተመደባችሁባቸው…
Read the full story at addis_news ↗