በጋዛ በጦርነት የተጎዳ ሕንፃ ተደርምሶ 21 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ
በጋዛ በጦርነት የተጎዳ ሕንፃ ተደርምሶ 21 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ በጦርነት የተጎዳ ሕንፃ በድንገት ተደርምሶ በውስጡ የነበሩ ቤተሰቦችንና ሌሎችን በርካቶችን ለሞት ዳርጓል። በጋዛ ሲቲ የወደቀው ሕንፃ ቢያንስ 21 ሰዎችን ሲገድል፣ ከሟቾቹ መካከል 8 ሕፃናት እንደሚገኙ ተገልጿል። ሕንፃው ከዚህ ቀደም በጦርነቱ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት አስጊ እንደነበረ ቢታወቅም፣ አማራጭ መጠለያ ባለመኖሩ ከ110 በላይ ሰዎች በሕንፃው ውስጥ ይኖሩ ነበር። በአደጋው 45 ሰዎች ከፍርስራሹ በሕይወት ሲወጡ፣ 14 ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል። በአደጋው ነፍስ የማዳን ሥራ በከባድ የመሣሪያ እጥረት ምክንያት ተስተጓጉሏል፤ አዳኞችም በእጃቸው ፍርስራሹን በመቆፈር ሰዎችን ለማውጣት ተገደዋል። የጋዛ ሲቪል መከላከያ በአካባቢው አሁንም ለመውደቅ አፋፍ ላይ የሆኑ ሌሎች ሕንፃዎች መኖራቸውን አስጠንቅቋል። ቤዛዊት…
Read the full story at zena24now ↗