በደቡብ አፍሪካ በሁለት ወራት ውስጥ 9ኛዋ ሴት ሞታ ተገኘች

ZENA24NOWneutral2026-09-17 16:50:12 UTC
AdYour ad here[email protected]

በደቡብ አፍሪካ በሁለት ወራት ውስጥ 9ኛዋ ሴት ሞታ ተገኘች በጆሃንስበርግ ምሥራቅ በሚገኘው ኤኩርሁሌኒ አካባቢ፣ በሁለት ወራት ውስጥ የ9ኛ ሴት አስክሬን መገኘቱ የደቡብ አፍሪካን ሕዝብ አስደንግጧል። ፖሊስ ክስተቶቹ እርስ በርስ የተያያዙ መሆናቸውን እያጣራ ቢሆንም፣ እስካሁን በአንድ ወንጀለኛ ወይም ቡድን መፈጸማቸውን አላረጋገጠም። የቅርብ ጊዜው የሴት አስክሬን የተገኘው ዛሬ ጠዋት በዳውን ፓርክ፣ ቦክስበርግ አካባቢ ሲሆን ማንነቷ ገና አልተለየም፤ ፖሊስም የሞቷን ምክንያትና ከቀደሙት ጉዳዮች ጋር ያላትን ግንኙነት እያጣራ ነው። ከዚህ በፊት የተገኙት ስምንት የሴቶች አስክሬኖችም በዚሁ የኤኩርሁሌኒ አካባቢ ተገኝተዋል። ፖሊስ አሁን ልዩ የምርመራ ቡድን አቋቁሞ ጉዳዩን በጥልቀት እየመረመረ ሲሆን፣ ማንኛውም መረጃ ያለው ሰው ለፖሊስ እንዲያሳውቅ ጥሪ ቀርቧል። ቤዛዊት አራጌ #ዳጉ_ጆርናል

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]