#Update
#Update በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ከሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ፣ የምዕራብ ጉጂ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " ኦነግ ሸኔ ኮሬ አካባቢንም እንደ ሎጂስቲክስ ምንጭ ይጠቀማል " በሚል የሰጡትን መረጃ የኮሬ ዞን አስተዳደር በብርቱ ተቃውሞና አውግዞ ነበር። ኃላፊው የተናገሩትን እና የሰጡትን መረጃ በይፋ እንዲያስተካክሉም በመግለጫ አሳስቦ ነበር። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኮሬ ዞንን መግለጫ ተከትሎ የምዕራብ ጉጂ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ዳምባን ስለ ጉዳዩ በድጋሚ አናግሯቸዋል። እሳቸውም በቃላቸው ፀንተው " ስለ ታጣቂው ቡድን የሎጂስቲክስ አቅርቦት የበለጠ ማብራሪያ እሰጣለሁ " ብለዋል። አቶ አየለ ፥ " ታጣቂ ቡድኑ ሎጂስቲክስ የሚያገኘው ከአጎራባቾቹ ወረዳ ነው፤ ቀለብ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗