እጅ የሰጡት የእኛ አይደሉም-ህወሓት‼️

ADDIS_REPORTERneutral2026-09-17 17:55:40 UTC
AdYour ad here[email protected]

እጅ የሰጡት የእኛ አይደሉም-ህወሓት‼️ ሕወሓት በወልቃይት-ተከዜ መስመር እጃቸውን የሰጡትን ከ260 በላይ ታጣቂዎቹን «የእኛ አይደሉም» ሲል ካደ። በወልቃይት፣ ተከዜ፣ አዲጎሹ እና ደደቢት መስመሮች በከባድ መሣሪያ የታገዘ ትንኮሳ ሲፈጽሙ የነበሩ ከ260 በላይ የሕወሓት አርሚ 17 አባላትና የመስመር አመራሮች ለአገር መከላከያ ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ሰጥተዋል። ይህን ተከትሎ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ እጃቸውን የሰጡት ተዋጊዎች የድርጅቱ አባላት አለመሆናቸውን ገልጸዋል። ከአካባቢው የተገኙ የመረጃ ምንጮች እንደሚጠቅሙት፣ የታጣቂ ቡድኑ አባላት በከባድ መሣሪያ በመታገዝ በወልቃይት እና ተከዜ ኮሪደር አዲስ ግጭት ለመቀስቀስ ሙከራ አድርገው ነበር። ሆኖም የመከላከያ ሠራዊቱ በወሰደው ፈጣንና የተቀናጀ የመልስ ምት እንቅስቃሴው በቅጽበት ሊከሽፍ ችሏል።…

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]